በአየር ንብረት ለውጥ ውስጥ የአካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር በአየር ንብረት ለውጥ ውስጥ የአካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር  (AFP or licensors)

ብዝሃ-ሕይወትን ከጥፋት ለመከላከል ያለን ጊዜ እያጠረ መምጣቱ ተገለጸ

ለንደን በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጥናት የሚያካሂድ የሳይንስ ሊቃውንት ቡድን፥ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ እና በብዝሃ-ሕይወት መመናመን ላይ ባካሄዱት ምርምር፥ በምድራችን የሚገኙ ነፍሳት ቁጥር በድንገት ሊቀንስ እንደሚችል እና ለቀውሱ ምላሽ ለመስጠት የቀረው ጊዜ እጅግ አጭር መሆኑን ገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዱባይ ከተማ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP28) ማጠቃለያ ላይ የተነሱ የሚቃረኑ ድምጾች፥ የተለያዩ ትችቶችን እና ከቅሪተ አካል ከሚገኝ የኃይል አጠቃቀም ወደ ታዳሽ የኃይል አጠቃቀም ፍትሃዊነት እና ሥርዓት ባለው መንገድ መሸጋገር እንደሚገባ አስተያየቶች ቀርበዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ስምምነት እርምጃውን ለማፋጠን በእነዚህ አሥርት አስቸጋሪ ዓመታት ውስጥ ከሳይንስ ጋር በተገናኘ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2050 ከቅሪተ አካል ነጻ የሆነ የኃይል ምንጭ አጠቃቀም ዕቅድ ማሳካት እንደሚገባ የሚጠይቀውን ስምምነት ብዙ ባለሙያዎች ቢስማሙትም ነገር ግን አገራት ያሳዩት ወቅታዊ ቁርጠኝነት ድንገተኛ አደጋን ለማስቆም በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።


በዱባይ ከተማ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን በጤና ምክንያት መካፈል ያልቻሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ ሥነ-ምሕዳርን በማስመልከት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2015 ዓ. ም. “ውዳሴ ላንተ ይሁን” በሚል ርዕሥ ሐዋርያዊ መልዕክት ይፋ ማድረጋቸውን በማስታወስ፥ በቅርቡ “ውዳሴ ለእግዚአብሔር ይሁን” በሚል ርዕሥ ይፋ ባደረጉት ሁለተኛው ሐዋርያዊ መልዕክታቸው፥ በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP15) ላይ የተደረሱት ስምምነቶች እስከ ዛሬ በተግባር እንዳልተረጎሙ ገልጸው፥ መንግሥታት የጋራ ጥቅምን ከማስቀደም ይልቅ አገራዊ ጥቅሞች ላይ ማትኮራቸውን ተናግረዋል።

“ውዳሴ ለእግዚአብሔር ይሁን” የሚለው ሁለተኛው የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ መልዕክት የአየር ንብረት ቀውሱን መቅረፍ እንደሚገባ አስቸኳይ ጥሪ በማቅረብ፥ በተፈጥሮ ላይ የደረሰው የማይቀለበስ ጉዳት በሰው ልጅ ጥፋት እንደሆነ አስረድቷል። ከጥፋተኛነት ጋር ተያይዞ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ የውሳኔ አሰጣጥ አስፈላጊነት ግንዛቤ እየጨመረ ቢመጣም፥ በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ (ዩሲኤል) የሳይንስ ሊቃውንት ቡድን በቅርቡ ያደረገው ጥናት ተጨማሪ እርምጃዎች በአስቸኳይ እንደሚያስፈልጉ አጉልቷል።

ብዝሃ-ሕይወት የጋራ መኖሪያ ምድራችንን ከጥፋት ይጠብቃል።
ብዝሃ-ሕይወት የጋራ መኖሪያ ምድራችንን ከጥፋት ይጠብቃል።

የዝርያዎች ብዛት በድንገት ሊቀንስ ይችላል

የተማራማሪዎች ቡድን የአየር ንብረት ትንበያዎችን በመጠቀም በዓለም ዙሪያ ያሉ የተወሰኑ አካባቢዎችን ወቅታዊ እና የወደፊቱን የሙቀት መጠን በማነፃፀር ባቀረነው ሪፖርቱ፥ ከ35,000 የሚበልጡ ዝርያዎችን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሊያጋጥማቸው እንደሚችል፥ “ኔቸር”፣ “ኢኮሎጂ” እና “ኢቮሉሽን” በተባለው ጥናታዊ መጽሔት ላይ ይፋ አድርጓል። ለተወሰኑ ፍጥረታት ለኑሮ የማይመች የጂኦግራፊያዊ ክልል ስፋት በድንገት ሊጨምር እንደሚችልም ደርሰውበታል።

“አሥር ዓመት አጭር ጊዜ ነው" ያለው የጥናቱ መሪ አሌክስ ፒጎት፥ ብዙ ዝርያዎች ፕላኔቷ ላይ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዓመታት መቆየታቸውን ገልጸው፥ ፈጣን ለውጦችን እየተስተናገዱ መሆናቸውን አስረድተዋል።እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፥ ሁኔታው የብዝሃ ሕይወት ቁጥር ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ቀስ በቀስ እንዲቀንስ ከማድረግ ይልቅ በድንገት ሊቀንስ እንደሚችል ታውቋል።

የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን መሪ አሌክስ ፒጎት፥
የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን መሪ አሌክስ ፒጎት፥

ምላሽ ለመስጠት ጊዜ የለውም!

ከቅድመ-ኢንዱስትሪ ጊዜ ጀምሮ ዓለም 1.2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ አካባቢ ሙቀት እንዳለው እና ይህም በስነ-ምህዳር ላይ ተጽእኖ እንዳለው ቀድሞውኑ ይታወቃል። “በጣም ሞቃታማ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ በርካታ ፍጥረታት እየሞቱ ሌሎች ወደ ቀዝቃዛ አካባቢዎች በመሄድ ተስማሚ የሆኑ የመቆያ ሥፍራዎችን በማግኘት ላይ ናቸው" ሲል ፒጎት ገልጿል። አክሎም የባህሪ ለውጦችን እየተመለከቱ እንደሆነ ገልጸው፥ ፍጥረታት በዓመቱ ውስጥ ቁልፍ የሕይወት ኡደት ክንውኖችን በሚያካሂዱበት ወቅት እንደሚለወጡ አስረድቷል።

በይነ መንግሥታት (IPCC) በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ማካሄደው ውይይት መሠረት፥ የሙቀት መጠን ወደ ሁለት ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚያድግ ከሆነ ምድራችን ከ 20% በላይ ዝርያዎችን ሊያጣ እንደሚችል ፒጎት አስጠንቅቋል። እነዚህን ምክንያቶች ከፒጎት እና ባልደረቦቹ ውጤቶች ጋር በማጣመር ለሁኔታው አጽንዖት መስጠት እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን፥ ፒጎት በገለጻው "አሁን እየተከሰቱ ያሉትን ለውጦች እና በመንገድ ላይ ለሚመጡት ለውጦች ዝግጁ አይደለንም" ብሏል። በድንገት የሚከሰቱ ለውጦች የበለጠ እንደሚፈታትን፥ ሁኔታዎች አጥንቶ ምላሽ ለመስጠት ያለው ጊዜ ውስን መሆኑን ተመራማሪው ገልጿል።

በፔሩ ተራራዎች የሚገኙ የአትክልት እና የአእዋፍ ዝሪያዎች
በፔሩ ተራራዎች የሚገኙ የአትክልት እና የአእዋፍ ዝሪያዎች

የወደፊት አቅጣጫዎች

ተመራማሪዎቹ እነዚህ መረጃዎች ብዝሃ-ሕይወትን በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ እና የአስተዳደር ስልቶችን ለማዘጋጀት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተስፋ አድርገዋል። አንዳንድ የባሕር ውስጥ ተክሎች ከሌሎቹ በተሻለ ሁኔታ ሳይጠወልጉ ወይም የመጥፋት አደጋ ሳያጋጥማቸው መቆየት እንደሚችሉ ፒጎት ተናግሮ፥ የተክሎችን ባህሪያት መለየቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሙከራዎችን ለመድገም አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግሯል።

በባሕር ውስጥ ተክሎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ እንደ አሳ ማጥመድ ወይም የግብርና ማዳበሪያዎች፥ በተለይ ለጽዳት ክስተቶች ተጋላጭ እንደሚሆኑ ሳይንቲስቶቹ ጠቁመው፥ “በባሕር ውስጥ ተክሎች ላይ የተደቀኑ ተጨማሪ ስጋቶችን መቀነሱ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላቸውን የመቋቋም አቅም ይጨምራል" ሲል ፒጎት አክሏል። ተመራማሪዎቹ እንደተገለጹት፥ “እነዚህን እና ሌሎች ስጋቶችን መቀነሱ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ነገር ግን ሥነ-ምህዳሮችን ከጥፋት ለመታደግ ከፈለግን ‘የግሪን ሃውስ’ ጋዝ ልቀታችንን በፍጥነት እና በቋሚነት ከመቀነስ የተሻለ ሌላ ምንም አማራጭ የለም" ሲሉ ተናግረዋል።

“ድንገተኛ የብዝሃ-ሕይወት መመናመን የተመዘገበበት የባሕር ውስጥ ተክል ብቻ አይደለም” ያሉት ተመራማሪዎቹ፥ ሌላው ምሳሌ በአውስትራሊያ ሰሜናዊ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ክልሎች ውስጥ በሚኖሩት የፍራፍሬ ዝርያ እና የሌሊት ወፍ  ላይ አስገራሚ ምልክት መታየቱን ገልጸዋል።

የባሕር ውስጥ ብዝሃ-ሕይወት
የባሕር ውስጥ ብዝሃ-ሕይወት

ኩዊንስላንድ እንደ ጎሮግሮሳውያኑ በ 2018 ዓ. ም. ከ42 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ በሆነ ኃይለኛ የሙቀት ማዕበል ተመታ እንደ ነበር ፒጎት ተናግሮ፥ በዚህ የሙቀት መጠን ከጠቅላላው ቁጥር አንድ ሦስተኛው ማለትም ከ 25,000 በላይ የሌሊት ወፎች በአንድ ቀን ውስጥ መሞታቸውን እና ይህ የአየር ለውጥ የፍጥረታትን የመላመድ ችሎታን የሚከለክለው ድንገተኛነት መሆኑን የሳይንስ ሊቃውንት አሳስበዋል።

አሁን ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ እና የብዝሃ-ሕይወት መጥፋት ቀውሶችን በብቃት ለመቅረፍ ከዝርያው ቁጥር ድንገተኛ መቀነስ አንጻር የላቀ የማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን እና ትንበያዎች ሊኖሩ እንደሚገባ ተመራማሪዎቹ ጠይቀዋል። “በእርግጥ የምንፈልገው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፍጥረታት ምን ያህል ተጽዕኖ እንደሚያሳድርባቸው በመተንበይ ድንገተኛ መመናመን መቼ እንደሚሆን ለመገመት ነው” ሲል ፒጎት አስረድቷል።

ሳይንቲስቶቹ ተፈጥሮን ከጥፋት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበው፥ ፒጎትም በበኩሉ “አሁን ካለው በለጠ እና በተሻለ መንገድ እንክብካቤ ልናደርግላቸው ይገባል” ብሏል። "የተጎዱ የሥነ-ምህዳር አካባቢዎችን መጠበቅ እንደሚገባ፥ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከማቸ የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን መገደብ የአየር ንብረት ለውጥን ስለሚቀንስ እና ብዝሃ ሕይወትም ወደ ቀዝቃዛማው አካባቢዎች በመዘዋወር ቁጥራቸው እንዲያድግ ያደርጋል” ሲል አስገንዝቧል።

ለከባድ አደጋ የተጋረጡ የሱማትራን ዝሆን እና ጥጃዋ
ለከባድ አደጋ የተጋረጡ የሱማትራን ዝሆን እና ጥጃዋ

በአየር ንብረት ለውጥ እና በብዝሃ ሕይወት መጥፋት መካከል ያለው ግንኙነት

ፒጎት፥ ዓለም በአሁኑ ጊዜ ሁለት ዋና ዋና ቀውሶች እንዳሉት፥ እነርሱም የአየር ንብረት ለውጥ እና የብዝሃ-ሕይወት መጥፋት እንደሆኑ ገልጾ፥ “እነዚህ በተፈጥሯቸው እርስ በርስ የተያያዙ እና በተወሰነ ደረጃ እንደ የመሬት አጠቃቀም ለውጥ እና የደን መጨፍጨፍ ባሉ ተመሳሳይ ሂደቶች የሚመሩ ናቸው" ሲል አስረድቷል።

“የመሬት አጠቃቀም ለውጥ እና የደን መጨፍጨፍ ለአየር ንብረት ለውጥ ዋና መንስኤዎች ናቸው” ያሉት ተመራማሪዎቹ፥ 20% የሚሆነው የሞቃታማ ጋዝ ልቀቶች ለአየር ንብረት ለውጥ ዋና ለብዝሃ-ሕይወት መጥፋት ዋና ዋና መንስኤዎች እንደሆኑ ተመራማሪዎቹ ገልጸው፥ የአየር ንብረት ለውጥ በብዝሃ ሕይወት መጥፋት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ወደፊትም እየተፋጠነ እንደሚሄድ ጠቁመዋል። "ምድርን በምናሞቅበት ጊዜ ዝርያዎችን እናጣለን" በማለት የሚከራከረው ፒጎት፥ በያዝነው ክፍለ ዘመን ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ለብዝሃ ሕይወት መጥፋት ዋነኛ መንስኤ ይሆናል ብለን እናስባለን" በማለት ተናግሯል።

የአየር ንብረት ቀደም ባሉት ጊዜያት ውስጥ ብዙ ጊዜ ቢለዋወጥም፥ አሁን ያለው ፍጥነት አሳሳቢ እንደሆነ እና 1.2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሙቀት መጨመር ብዙም እንደማይሰማ ነገር ግን አሁን ባለንበት ፍጥነት ከቀጠለ እስከ ምእተ ዓመት መጨረሻ ከ2.5 እስከ 3 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሙቀት መጠን እንደሚጠብቀን ፒጎት ተናግሮ፥ ለመጨረሻ ጊዜ ተመሳሳይ የሙቀት መጠን ያጋጠሙን የዛሬ 3 ሚሊዮን ዓመታት አካባቢ እንደነበር ተመራማሪዎቹ አስታውሰዋል። “በመሠረቱ የ3 ሚሊዮን ዓመታትን የምድር ታሪክ ወደሚቀጥሉት ጥቂት አሥርት ዓመታት እየገለበጥን ነው” ያለው ፒጎት፥ ይህም እጅግ ፈጣን የለውጥ ፍጥነት እና ለመቋቋም ዝግጅት ያልተደረገበት የለውጥ ፍጥነት እነድሆነ አስረድቷል።

በፕላኔቷ ላይ የሚኖሩት 8 ሚሊዮን ዝርያዎች ከ8 ቢሊዮን ሰዎች ጋር አብረው እንደሚኖሩ ፒጎት ገልጾ፥ የግብርና መሬቶች ለሰፊ የከተማ መኖሪያነት መቀየራቸው ለብዝሃ-ሕይወት ውድቀት ዋነኛ መንስኤ እንደሆነ ፒጎት አክሎ አስረድቷል። እንደ ሳይንቲስቶቹ ገለጻ፥ የተለያዩ ዝርያዎች የመኖሪያ ቦታቸውን ማጣት መጭውን ጊዜ መላመድን እንደሚከለክል እና ለአየር ንብረት ለውጡ ምላሽ ለመስጠት ዝርያዎቹ ወደ ቀዝቃዛማው አካባቢ እንደሚሰደዱ አስረድተዋል።

"ብዝሃ-ሕይወት ለሰብዓዊ ማህበረሰብ እጅግ ብዙ ጥቅሞችን እንደሚሰጥ ሁል ጊዜ ማስታወስ አለብን" ሲል የተናገረው ፒጎት፥ እነዚህን ሥርዓቶች ማጣት ማለት የሚሰጡትን ጥቅሞች ማጣት ማለት ነው" ሲል አስረድቷል።

በኮሎምቢያ ውስጥ የሚገኝ የአበባ ዝሪያ
በኮሎምቢያ ውስጥ የሚገኝ የአበባ ዝሪያ

 

 

28 December 2023, 17:35