ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ መንፈስ ቅዱስ ድፍረት፣ ተስፋ እና እምነት ይሰጠናል አሉ!
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በግንቦት 15/2013 ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደበት የጴንጤቆስጤ በዓል ተክብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ባደረጉት አስተንትኖ መንፈስ ቅዱስ ድፍረት ፣ ተስፋ እና እምነት ይሰጠናል ማለታቸው ተገልጿል።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ (2፡1-11) ኢየሱስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ በዓል ከተከበረ ከ50 ቀናት በኋላ በኢየሩሳሌም ምን እንደ ተከሰተ ይተርካል። ደቀ መዛሙርቱ በላይኛው ክፍል ውስጥ ተሰብስበው ነበር፣ ድንግል ማርያምም ከእነርሱ ጋር ነበረች። ከላይ የተጠቀሰው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እስኪያገኙ ድረስ ከሙታን የተነሳው ጌታ በከተማው ውስጥ ሆነው እንዲቆዩ ነግሯቸዋል። እናም ይህ በድንገት ከሰማይ ሲመጣ በሰሙት “በድምፅ” ተገለጠ ፣ እነሱ የነበሩበትን ቤት “እንደ ኃይለኛ ነፋስ” በሆነ መልኩ ቤቱን ይሞላዋል (የሐዋርያት ሥራ 2፡ 2)። ስለሆነም እሱ እውነተኛ ነገር ግን ምሳሌያዊ ልምድን ይመለከታል። የሆነ ነገር የተከሰተ ነገር ግን ለህይወታችን በሙሉ ምሳሌያዊ መልእክት ይሰጠናል።
ይህ ተሞክሮ መንፈስ ቅዱስ እንደ ጠንካራ እና በነፃነት እንደሚፈስ ነፋስ መሆኑን ያሳያል። ማለትም እሱ ጥንካሬን አምጥቶ ነፃነትን ይሰጣል-ጠንካራ እና በነፃነት የሚፈስ ነፋስ ነው። እሱ ሊቆጣጠረው ፣ ሊያቆመው፣ ሊለካውም የሚችል ማንም የለም። እንዲሁም የእርሱ መመሪያ አስቀድሞ ሊታወቅ አይችልም። እሱ በእኛ ሰብአዊ ፍላጎት ውስጥ ሊገባ አይችልም - እኛ ሁሌም ነገሮችን ለማቀናበር እንሞክራለን - እሱ በእኛ ዘዴዎች እና በእኛ ቅድመ-ግንዛቤዎች ውስጥ እራሱን እንዲቀርፅ አይፈቅድም። መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ እና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ይወጣል እናም በቤተክርስቲያኑ ላይ ይፈሳል፤ እርሱ ለአእምሮአችን እና ለልባችን ሕይወትን በመስጠት በእያንዳንዳችን ላይ ይነፋል። ጽሎተ ሐይማኖት እንደሚገልጸው-እርሱ “ሕይወት ሰጪ ጌታ” ነው። እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ ኃይል አለው ሕይወትንም ይሰጣል።
በጴንጤቆስጤ ዕለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አሁንም ግራ የተጋቡ እና ፍርሃት ነበራቸው። አደባባይ ወጥቶ ለመስበክ ገና ድፍረቱ አልነበራቸውም። እኛም አንዳንድ ጊዜ በአካባቢያችን በሚገኙ መከላከያ ግድግዳዎች ውስጥ መቆየትን እንመርጣለን። ጌታ ግን እንዴት እንደሚቀርበን ያውቃል የልቦቻችንንም በሮች ይከፍታል። እርሱ እኛን የሚያስጨንቀንን እና ማመንታቶቻችንን ሁሉ የሚያሸንፈን ፣ ጋርዶ የያዘንን ነገሮች የሚያፈርስ ፣ የሐሰት ማረጋገጫዎቻችንን የሚያፈርስ መንፈስ ቅዱስን በላያችን ላይ ይልክልናል። መንፈስ ቅዱስ በዚያ ቀን ከሐዋርያት ጋር እንዳደረገው አዲስ ፍጥረታት ያደርገናል-እርሱ አዲስ ያደርገናል ፣ ያድሰናል።
መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ከእዚህ ቀድም እንደነበሩት አልነበሩም - እሱ ቀየራቸው ፣ እነሱ ወጥተው ኢየሱስ እንደተነሳ መስበክ ጀመሩ ፣ ኢየሱስ እንደተነሳ ለመስበክ ፣ ጌታ ከእኛ ጋር እንዳለ ለመስበክ፣ እያንዳንዱም በራሳቸው ቋንቋ ተረድተዋል፣ ማስረዳትም ጀምረዋል። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ሁለንተናዊ ነው፤ ባህላዊ ልዩነቶችን ፣ የአስተሳሰብ ልዩነቶችን አያስወግድም። እሱ ለሁሉም ነው ፣ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ባህል ፣ በራሱ ቋንቋ ይገነዘበዋል። መንፈስ ልብን ይለውጣል ፣ የደቀመዛሙርቱን አመለካከት ያሰፋል። ማሰብ እና መኖር የለመዱባቸውን ባህላዊ ድንበሮች እና ሃይማኖታዊ ድንበሮችን በማለፍ ታላላቅ ፣ ገደብ የለሽ የእግዚአብሔርን ሥራዎች ለሁሉም ሰው እንዲያሳውቁ ያስችላቸዋል። ሐዋርያቱ የእያንዳንዳቸውን ባህል እና ቋንቋ የማዳመጥ እና የመረዳት አቅማቸውን በማክበር ሌሎችን እንዲደርሱ ያስችላቸዋል (የሐዋርያት ሥራ 2፡5-11)። በሌላ አገላለጽ መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ሰዎችን እንዲገናኙ ያደርጋቸዋል፣ የቤተክርስቲያኗን አንድነት እና ሁለንተናዊነትን ያሳካል።
እናም ዛሬ ይህ እውነት ዛሬም ቢሆን የሚነግረን ነገር አለ፣ ይህ የመንፈስ ቅዱስ እውነታ ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሁል ጊዜ መከፋፈልን የሚሹ ትናንሽ ቡድኖች ካሉ ከሌሎች ጋር ለመለያየት የሚፈልጉትን ሰዎች ካሉ ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳልሆን ይነግረናል። የእግዚአብሔር መንፈስ ስምምነት ነው ፣ አንድነት ነው ፣ ልዩነቶችን አንድ ያደርጋል። የጄኖቫ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አንድ ጥሩ ካርዲናል ቤተክርስቲያን እንደ ወንዝ ናት ብለው የነበረ ሲሆን ዋናው ነገር ወደ ውስጥ መሆን ነው በተቃራኒ መቆ አስፈላጊ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ አንድነትን ይፈጥራል። እሱ የወንዙን ምስል ተጠቅሟል።፡ አስፈላጊው ነገር በውስጣችን መሆን ፣ በመንፈስ አንድነት ውስጥ መሆን ፣ እና በዚህ በኩል ወይም በሌላ መልኩ የሚጸልዩትን በእዚያ እና በእዚህ በኩል ያሉትን ሰዎች በአንድነት ማምጣት ነው። በጴንጤቆስጤ ዕለት መንፈስ ቅዱስ እንዳሳየው ቤተክርስቲያን ለሁሉም ፣ የሁሉም እንደ ሆናች ነው።
መንፈስ ቅዱስ በብዛት እንዲወርድ ፣ የአማኞችን ልብ እንዲሞላ እና የፍቅሩን እሳት በሁሉም ሰው እንዲያነድ የቤተክርስቲያን እናት የሆናችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ታማልድ ዘንድ እንማጸናት።